ክታብ (Ketab)

በሰው ወይንም በከብት ዐንገት የሚንጠለጠል የጽሕፈት ሽብልል ኹኖ በያይነቱ ጽሑፍና ያስማት ሥዕል ያለበት ለሰው ዓይን ለራስ ምታት ለፍልጠት ለቍርጠት ለውጋት ለቍርጥማት መድሐኒትነት ጠንቋዮች የሚፅፉት ፤የሚሥሉት እንዲሁም ባለድጕስ አስማትና ሥራሥር ያለበት ፤ በአንገት የሚታሰር ከቆዳ የተሰራ መድሐኒት ነው።